Social Icons

Wednesday, August 21, 2013

የአዲስ አበባ የባቡር መስመር ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ

የአዲስ አበባ የባቡር መስመር ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እየተከናወነ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታወቀ
አስሩንም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች አቋርጦ የሚያልፍ ባለሁለት መስመር ሃዲድ ግንባታ ነው በመከናወን ላይ ያለው፡፡የቀላል ባቡሩ ግንባታ ርዝመቱ ባጠቃላይ 72 ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፡፡

በ41 ባቡሮች ስራ የሚጀምረው መስመር በሰዓት እስከ 60ሺ ሰዎችን የማመላለስ አቅም ሲኖረው በቀን ለ18 ሰዓታት አገልግሎቱን ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

እያንዳንዱ ባቡር ቢያንስ 3 ፉርጎዎች የሚኖሩት ሲሆን አንዱ ፉርጎ ከ200 በላይ መቀመጫዎች ይኖሩታል፡፡

የአዲስ አበባው ቀላል ባቡር በሰአት 120 ኪሎሜትሮች የመጓዝ አቅም ሲኖረው በባቡር ማቆሚያ ጣቢያ ላይ ቢያንስ በየ5 ደቂቃው ይደርሳል፡፡


የአዲስ አበባ ቀላል የኤለየክትሪክ ባቡር ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ሲነፃፀር የድምፅና የአየር ብክለት የማያስከትል በመሆኑ፣ የኤለየክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የማያሰጋው በመሆኑ፣ ማየት ለተሳናቸው ወገኖች ጠቋሚ ቴክኖሎጂ ያለው በመሆኑና በምቾቱ ለየት ያደርገዋልም ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት ከያዛቸው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መሀከል ከ2000 ኪ.ሜ በላይ የባቡር መስመር መገንባት አንዱና ዋነኛው የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ ይታወቃል፡፡

No comments:

Post a Comment